ፈፍ
ፈ ፉ ፊ ፋ ፌ ፍ ፎ ፏ
የአቡጊዳ ታሪክ | |||||
---|---|---|---|---|---|
አ | በ | ገ | ደ | ||
ሀ | ወ | ዘ | ሐ | ጠ | የ |
ከ | ለ | መ | ነ | ሠ | ዐ |
ፈ | ጸ | ቀ | ረ | ሰ | ተ |
ፈፍ (ወይም አፍ) በጥንታዊ አቡጊዳ ተራ 17ኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያ በዕብራይስጥ ፊደሎች በሶርያም 17ኛው ፊደል "ፔ" ይባላል። በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል "ፋእ" ተብሎ በ"አብጃድ" ተራ 17ኛ ነው።
ታሪክ
ተመሳሳይ ግብፃዊ ስዕል «ረ» | ቅድመ-ሴማዊ | ሣባ | ግዕዝ | ||
---|---|---|---|---|---|
| ፈ |
የፈፍ መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የአፍ ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። አጠራሩ ግን «ረ» ነበር። በግብፅ የሠሩት ሴማውያን ግን በቋንቋቸው «ፔ» ስላሉት፣ ይህ ስዕል «ፕ» ሆኖ እንዲሰማ መጣ። ኋላም «ፍ» የምለውን ተናባቢ ደግሞ አሰማ።
ከነዓን | አራማያ | ዕብራይስጥ | ሶርያ | ዓረብኛ |
---|---|---|---|---|
פ,ף | ﻑ |
የከነዓን «ፔ» እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ «ፔ» የአረብኛም «ፋእ» ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት «ፒ» (Π, π) አባት ሆነ። እሱም የላቲን አልፋቤት (P p) እና የቂርሎስ አልፋቤት (П п) ወላጅ ሆነ። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የ«ፈፍ» ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር ፹ (ሰማንያ) ከግሪኩ π በመወሰዱ እሱም የ«ፈ» ዘመድ ነው።
🔥 Top keywords: ዋናው ገጽልዩ:Searchስዕል:Keristo1.pdfኢትዮጵያሚካኤል2ኛው ዓለማዊ ጦርነትሥርዓተ ነጥቦችፋይዳ መታወቂያሥነ-ፍጥረትአበበ ቢቂላአማርኛዓፄ ቴዎድሮስSpecial:Searchእርዳታ:ይዞታገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችውክፔዲያጥላሁን ገሠሠቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴኤችአይቪልዩ:RecentChangesየአድዋ ጦርነትግራኝ አህመድኃይሌ ገብረ ሥላሴሀዲስ ዓለማየሁየቅድስት ድንግል ማርያም ስሞችመጽሐፍ ቅዱስሥላሴየዋና ከተማዎች ዝርዝርአፋር (ክልል)የቃል ክፍሎችበዓሉ ግርማኢየሱስቅዱስ ጊዮርጊስ (ሰማዕት)አዲስ አበባቅዱስ ያሬድትግራይ ክልልእስራኤልየኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን