ዶሪ

ራስ ዶሪኢትዮጵያ ዘመነ መሳፍንትበጌምድር ራስ፣ ለጥቂትም ወራት በ1823 ዓም የየጁ ስርወ መንግስት እንደራሴ ነበሩ። የራስ ጉግሣ ልጅና የራስ ማርዬ ወንድም ነበሩ።

ወንድማቸው ራስ ይማም ከአረፉ በኋላ፣ ራስ ማርዬ ማዕረጉን ቶሎ ይዘው ነበር፣ ዶሪ በጦር ምንም ቢቃውሙዋቸው።[1]

ዶሪ በየጁ ኦሮሞ ጦርነት ከማርዬ ጋር በደብረ አባይ ውግያ ታገሉ። ራስ ማርዬ በውግያው ተገድለው ዶሪና ሥራዊታቸው በትግራይ ውስጥ በዘበዙ።[2]

አክሱም ከተማ ዙሪያ ባለው አገር ቤት እየዘረፉ፣ ራስ ዶሪ ድንገት ታመሙ። በፈረንጅ ተጓዡ ሳሙኤል ጎባ ምስክር መሰረት፣ ያንጊዜ ራስ ዶሪ በሎሌዎቹ ላይ የታማኝነት ጥያቄ አንሥተው ግማሾቹ ሎሌዎች እንዲታሠሩ አዘዙ። ወደ ደብረ ታቦር ተመልሰው በክረምቱ ሞቱ።[3] እንደራሴው እየሆኑ ያደረጉት አንድያ ትልቅ ሥራ ንጉሠ ነገሥቱን ዓፄ ጊጋር ከዙፋናቸው አወርደው በፈንታቸው 4ኛው ኢያሱ መሾማቸው ነበረ።

በዘመነ መሳፍንት ዘና መዋዕሎች ዘንድ፣ የራስ ዶሪ ጭፍሮች ከትግራይ እየተመለሱ ብዙዎች ርበው ፈረሶቻቸውን ለወተት ወይም ለዳቦ ሸጡ። ዶሪ ጽድቅ እንደራሴ በመሆናቸው ጭፍራው ዳቦ ወይም ወተት ከሰው የቃመ እንደ ሆነ የበዳዩ ፈረስ ለተበዳዩ ይሰጠው ነበር ይላል። ደጃዝማቾች ክንፉ እና አመዴ ሁከት እንዳያንሱ ታሰሩ ይላል፤ ከዚያ ዶሪ ታመው በሰኔ ወር ዓረፉ ይላል።[4]

ዋቢ ምንጮች

ቀዳሚው
ማርዬ
የጁ ስርወ መንግስት
1823 ዓም
ተከታይ
ዓሊ (ትንሹ)