ይማም

ራስ ይማምኢትዮጵያ ዘመነ መሳፍንት ከ1817 እስከ 1820 ዓም ድረስ የበጌምድር ራስ፣ የየጁ ስርወ መንግስት እንደራሴ ነበሩ። የራስ ጉግሣ ልጅ ነበሩ።

አባታቸው ራስ ጉግሣ በ1817 ዓም ዐርፈው ይማም እንደራሴ በሆኑበት ወቅት ወንድማቸው ማርዬ ወዲያው ዐመጹባቸው።[1]

በጸሐፊው አቶ ትሪሚንግሃም ዘንድ፣ ራስ ይማም ለተዋሕዶ እምነት ሳይሆን ለእስልምና ድጋፋቸውን በገሐድ ሰጡ።[2] ከዚህም በላይ አቡነ 3ኛ ቅሪሎስ በሦስት ልደት ክርክር ውስጥ በዕርቅ ሲገቡ፣ ራስ ይማም ተናድደውባቸው ቅሪሎስን ወደ ሐይቅ ሐይቅ ገዳም በግዞት ሰደዱዋቸው።[3]

ራስ ይማም በጎጃም በደጃዝማች ጎሹ ዘውዴ ላይ እየዘመቱ፣ ደጃዝማች ሃይለ ማርያም ከስሜን ግዛት ገሥግሠው ወደ ጎንደር ደርሰው ንጉሠ ነገሥቱን ዓፄ ጊጋርን ገልብጠው በምትካቸው ዓፄ 3ኛ ባዕደ ማርያም አስነሡ። ራስ ይማም ይህን በሰሙበት ጊዜ፣ በድንግል በር በኩል ተመልሰው ደጃች ሃይለ ማርያምን እስከ ዋልደባ ድረስ አባረሩት። በዚያ ሥፍራ ለሦስት ቀን ከታገሉ በኋላ ደጃች ሃይለ በወገራ በኩል ወደ ስሜን ግዛት ሸሽተው ዓረፉ። ይህም ስለሆነ ራስ ይማም አጼ ጊጋርን ወደ ዙፋናቸው ሊመልሷቸው ቻሉ።[4]

ጸሐፊው አቶ ስቨን ሩበንሶን እንደ ገለፀው፣ የደጃች ሃይለ ማርያም ልጅ ውቤ ሃይለ ማርያም በውግያው ተማረከ፣ የይማም ወዳጅ ደጃች ሜሩ ዘደምቢያ ግን ልጁን ነጻ እንዲያውጡት አሳመኑዋቸው። ከትንሽ ጊዜ በኋላ ውቤ ደጃች ሆነው ከራስ ይማም ጋር ተባብረው ደጃች ጎሹንና ደጃች ሜሩን በኮሶበር ውጊያ በ1820 ዓም አሸነፏቸው። ጎሹ ወደ ጎጃም እየሸሹ፣ ሜሩ ከውግያው ቀጥሎ በወታደር ተገደለ።[5] በኋላ ራስ ይማም በደብረ ታቦር በግፍ ሞቱ።[4]ታቦር እየሱስ ቤተክርስቲያን ተቀብረዋል።[6]

ዋቢ ምንጮች

ቀዳሚው
ጉግሣ
የጁ ስርወ መንግስት
1817-1820 ዓም
ተከታይ
ማርዬ