የዓለም ጽሕፈቶች

ዛሬውን በሰፊ ጥቅም ላይ ያሉት የዓለም ጽሕፈቶች በ5 ዋና መደቦች ሊካፈሉ ይችላሉ። እነዚህም፦

  • ሎጎግራም (የቃል ምልክቶች)
  • አብጃዶች (የተናባቢ ምልክቶች)
  • አልፋቤቶች (የተናባቢ እና የአናባቢ ምልክቶች)
  • ሲላባሪ (ሌሎች የክፍለ-ቃል ምልክቶች)
  • አቡጊዳዎች (ተመሳሳይ የክፍለ-ቃል ምልክቶች)
በሰፊው ለመመልከት ስዕሉን ይጫኑ
  ሃንጉል (የኮርያ ጽሕፈት)
  ሌሎች አልፋቤቶች
  የዐረብ ጽሕፈት (አብጃድ)
  ሌሎች አብጃዶች
  ደቫናጋሪ ጽሕፈት ('አቡጊዳ' የተባለ)
  ሌሎች 'አቡጊዳዎች'
  የክፍለ-ቃል ምልክቶች (ሲላባሪ)
  የቻይና ጽሕፈት (ሎጎግራፊክ)

ሎጎግራፊክ ጽሕፈቶች

ሎጎግራፊክ ጽሕፈቶች እያንዳንዱ ምልክት ወይም ሎጎግራም ለአንድ ቃል ይቆማል። የግብጽ ሃይሮግሊፎች መጀመርያ ከሎጎግራም (ስዕሎች) ብቻ ተሠራ። ዕጅግ በጥንት ቅድመ-ታሪክ ዘመን ግን የተናባቢ ምልክቶች እና የክፍለ-ቃል ምልክቶች ተጨመሩለት።

በሌሎቹ ጥንታዊ ሎጎግራም ጽሕፈቶች ደግሞ እያንዳንዱ ምልክት ለቃል ወይም ለክፍለ-ቃል ሆኖ ይጻፍ ነበር። ከነዚህም የትንሹ እስያ ሃይሮግሊፍ፣ ኩነይፎርም ጽሕፈት፣ የማያ ሃይሮግሊፍ አሉ።

ኣሁን የቻይና ጽሕፈት እንዲሁም ከሎጎግራም ይሠራል። የቻይና ጽሕፈት ከቻይንኛ ጭምር ለሌሎች ልሳናት እንደ ቬትናምንኛ፣ ኮሪይኛ ቀድሞ ይጠቀም ነበር። ዛሬም የቻይና ምልክቶች በጃፓንኛ ጽሕፈት ደግሞ ይገኛሉ። በቻይና ዙሪያ ሌሎች ተመሳሳይ ጽሕፈቶች ዪ ጽሕፈት፣ ታንጉት ጽሕፈት፤ የናቂ ጽሕፈት ይገኛሉ።

ሲላቢክ ጽሕፈቶች

በሲላቢክ ጽሕፈቶች እያንዳንዱ ምልክት ለአንድ ክፍለ-ቃል ይጠቅማል።

በ'ጥሬ ሲላቢክ' ጽሕፈቶች፣ እነኚህ ምልክቶች ለአንድ ድምጽ አይመሳሰሉም። ስለዚህ «ቴ... ታ... ቶ...» የሚሉ ፊደላት ከቶ አይመሳሰሉም፣ ለምሳሌ በጃፓንኛ በሚጠቅመው «ካታካና» በሚባል ጽሕፈት፤ እነዚህ ድምጾች テ , タ, ト ይጻፋሉ። ጃፓንኛ ደግሞ ሌላ «ሂራጋና» በተባለ ሲላቢክ ጽሕፈት ሊጻፍ ይችላል።

ሌሎች ጥሬ ሲላቢክ ጽሕፈቶች በጥንት የቆጵሮስ ጽሕፈት (Mycaenaean Greek Linear B) እና ኩነይፎርም፤ ዛሬም፦

  • የዩግቱን ጽሕፈት (በአላስካ ለሚገኘው ዩፒክ ቋንቋ)
  • የጻላጊ ጽሕፈት (በአሜሪካ ለሚገኘው ጻላጊ ቋንቋ)
  • የአፋካ ጽሕፈት (በሱሪናም ለሚገኘው ንድዩካ ቋንቋ)
  • የኪካኩዊ ጽሕፈት (በሲዬራ ሌዎን ለሚገኘው መንዴ ቋንቋ)
  • የክፔሌ ጽሕፈት (በላይቤሪያ ለሚገኘው ክፐሌ ቋንቋ)
  • የቫይ ጽሕፈት (በላይቤሪያ ለሚገኘው ቫይ ቋንቋ)
  • ዘመናዊ ዪ ጽሕፈት (በቻይና ለሚገኘው ዪ ቋንቋ)
  • የኒው ሹ ጽሕፈት (በቻይና ለሚገኘው ያውኛ ቋንቋ)
  • የኤስካያን ጽሕፈት (በፊልፒንስ ለሚገኘው ኤስካያን ቋንቋ)
  • የዎሌያይ ጽሕፈት (በማይክሮኔዥያ ለሚገኘው ዎሌያይ ቋንቋ)

አቡጊዳዎች

በቋንቋ ጥናት በቅርቡ አቡጊዳ የሚለው ቃል ከኢትዮጵያ ልሳናት ተወስዶ ሌላ ትርጉም ተሰጥቶታል። በዚህ መደብ እያንዳንዱ ክፍለ-ቃል ለተመሳሳይ ድምጽ ተመሳሳይ ቅርጽ ኖሮት ይመሳሰላሉ። እያንዳንዱ ፊደል ከአንድ መሠረት ቅርጽ ጀምሮ በየአናባቢው ይለወጣል ማለት ነው። ስለዚህ ቴ... ቱ... ታ... (እንደ ግዕዝ ጽሕፈት) ሲመሳሰሉ ይታያሉ።

በዚህም መደብ ውስጥ ከኢትዮጵያ ፊደሎች ጭምር በሕንድ ዙሪያ የተገኙት ብራህሚክ ጽሕፈቶች (ዴቫናጋሪ ወዘተ.) እና የካናዳ ኗሪዎች ጽሕፈት ይከተታሉ።

አልፋቤቶች

አብጃዶች

በአብጃዶች እያንዳንዱ ምልክት ለአንድ ተናባቢ ይጠቅማል። አብጃዶች ከሁሉ አስቀድሞ የተለመደው የአልፋቤት አይነት ነበር። በመጀመርያ አብጃዶች አናባቢዎቹ አልተጻፉም ነበር። በዛሬው አብጃዶች ግን (የዕብራይስጥ አልፋቤት፣ የአረብኛ አልፋቤት ወዘተ...) አናባቢዎቹ በልዩ ልዩ ተጨማሪ ምልክታት ሊታዩ ይቻላል።

አብጃዶች ለሴማዊ ቋንቋዎች የተፈጠሩ ናቸው። ከሌሎች አብጃዶች መካከል፦

በቀድሞውም፦

  • የኡጋሪት አልፋቤት - (ሶርያ)
  • ቅድመ-ከነዓናዊ አልፋቤት (እስራኤል)
  • የፊንቄ / ጥንታዊ ዕብራይስጥ አልፋቤት (እስራኤል)
  • ጥንታዊ የአራማያ አልፋቤት (ሶርያ)
  • የጳርቴ አልፋቤት (ፋርስ)
  • የአቨስታ አልፋቤት (ፋርስ)
  • የሶግድያናውያን አልፋቤት (ዑዝበክስታን)
  • የማኒኬያውያን አልፋቤት (ፋርስ)
  • የናባታውያን አልፋቤት (ዮርዳኖስ)
  • የሳምራውያን አልፋቤት (እስራኤል)
  • የሣባውያን አልፋቤት (የመን)
  • ጥንታዊ የአግዓዝያን አልፋቤት (ኤርትራ)
  • የጣሙዲክ አልፋቤት (አረብያ)

ሙሉ ፊደላት

በሙሉ ፊደላት (ባለ-አናባቢ አልፋቤቶች) እያንዳንዱ ምልክት ለተናባቢ ወይም ለአናባቢ ይጠቅማል። ስሙ ከግሪክ አልፋቤት መጀመርያ 2 ፊደላት አልፋ እና ቤታ መጣ። የላቲን አልፋቤት ደግሞ ሙሉ ፊደል ነው። ከሌሎቹም ዛሬ፦

  • የንኮ አልፋቤት (በማሊጊኔ ለሚገኘው ማንዴ ቋንቋ)
  • የኦል ቸመጥ አልፋቤት (በሕንድ ለሚገኘው ሳንታሊኛ)
  • የምያው አልፋቤት (በቻይና ለሚገኘው ህሞንግ ቋንቋ)
  • የሊሱ አልፋቤት (በቻይና ለሚገኘው ሊሱ ቋንቋ]])
  • የቫህ አልፋቤት (በላይቤሪያ ለሚገኘው ባሣ ቋንቋ)


በጥንትም፦

  • ኦርኾን አልፋቤት - (ሞንጎልያ)
  • ጥንታዊ ሀንጋርኛ አልፋቤት (ሀንጋሪ)
  • የኡይጉር አልፋቤት (ቻይና)
  • የማንቹ አልፋቤት (ቻይና)
  • የትንሹ እስያ አልፋቤቶች (ቱርክ)
  • የኩማይ አልፋቤት (ግሪክ፣ ጣልያን)
  • የኤትሩስካውያን አልፋቤት (ጣልያን)
  • የቬኔቲክ አልፋቤት (ጣልያን)
  • የሩን አልፋቤት (ጀርመን)
  • የፋሊስካን አልፋቤት (ጣልያን)
  • የኦስካን አልፋቤት (ጣልያን)
  • የሜሳፒክ አልፋቤት (ጣልያን)
  • የግሪክ-ኢበራውያን አልፋቤት (እስፓንያ)
  • የጎታውያን አልፋቤት (ዩክሬን)
  • የግላጎሎቲክ አልፋቤት (ቡልጋሪያ)
  • የአቡር አልፋቤት (ሳይቤሪያ)
  • ኦጋም አልፋቤት (አይርላንድ)
  • የበይጣ ኩክዩ አልፋቤት (አልባንያ)
  • የኤልባሳን አልፋቤት (አልባንያ)
  • የኦስማንያ አልፋቤት (ሶማልያ)
  • የቦራማ አልፋቤት (ሶማልያ)

የቦፖሞፎ አልፋቤት በታይዋን ለቻይንኛ ሲጠቀም በከፊል ሲላቢክ ነው። በድሮ በእስፓንያ የነበሩ ጽሕፈቶች (የተርቴሶስ አልፋቤት ወዘተ.) ሙሉ ፊደሎች ሳይሆኑ በከፊል ሲላቢክ ነበሩ።

ደግሞ ይዩ