ዘይ

ዘ ዙ ዚ ዛ ዜ ዝ ዞ ዟ



አቡጊዳ ታሪክ

ዘይ (ወይም ዛይ) በአቡጊዳ ተራ ሰባተኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓንአራማያዕብራይስጥና በሶርያ ፊደሎች 7ኛው ፊደል "ዛይን" ይባላል። በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል "ዛይ" ተብሎ በ"አብጃድ" ተራ 7ኛ ነው።

አማርኛ ደግሞ "ዠ ዡ ዢ ዣ ዤ ዥ ዦ" ከ"ዘ..." ትንሽ ተቀይሯል።

ታሪክ

ተመሳሳይ ግብፃዊ ስዕልቅድመ-ሴማዊሣባግዕዝ
U7


የዘይ መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የመኮትኮቻ ስዕል ይመስላል። ለዚህም ምናልባት ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ "መር" ነበር።

ከነዓንአራማያ ዕብራይስጥሶርያዓረብኛ
ז


የከነዓን "ዛይን" እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ "ዛይን" የአረብኛም "ዛይ" ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት "ዜታ" (Ζ, ζ) አባት ሆነ፤ እሱም ላቲን አልፋቤት (Z, z) እና የቂርሎስ አልፋቤት (З, з) ወላጅ ሆነ። እነዚህ ሁሉ የ"ዘይ" ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር (ሰባት) ከግሪኩ ζ በመወሰዱ እሱም የ"ዘ" ዘመድ ነው።