ወልደያ

ወልደያ

ወልደያ ወይንም ወልዲያደሴ ሰሜን 120 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ከላሊበላ ደግሞ በደቡብ ምስራቅ ያለ በኢትዮጵያአማራ ክልል ከተማ ሲሆን በሰሜን ወሎና በወልዲያ ወረዳ ይገኛል። ከኢኮኖሚ አንጻር ለሕንጻ ስራ የሚያገለግል የኖራ ምርት በአካባቢው በትንሹ መካሄዱ በታሪክ ይጠቀሳል[1]

ወልደያ
ወልደያ ከተማ
አገር ኢትዮጵያ
ክልልአማራ ክልል
ዞንሰሜን ወሎ
ከፍታ2,112 ሜትር
የሕዝብ ብዛት
   • አጠቃላይ46,139
ወልደያ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ወልደያ

11°49′ ሰሜን ኬክሮስ እና 39°36′ ምሥራቅ ኬንትሮስ

ወልድያ ከተማ በ1770ዎቹ በታላቁ ራስ ዓሊ የንግሥናዘመን የተመሰረተች፤ 4 ዋና ዋና የአውራ ጎዳና መንገዶችየሚገናኙባት ለአብዛሃኛው የሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ ክፍሎች መገናኛ ከተማ ነች፡፡

ወልድያ

ወልድያ ከተማ በ1770ዎቹ በታላቁ ራስ ዓሊ የንግሥናዘመን የተመሰረተች፤ 4 ዋና ዋና የአውራ ጎዳና መንገዶችየሚገናኙባት ለአብዛሃኛው የሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ ክፍሎች መገናኛ ከተማ ነች፡፡ መገኛነቷን ስንቃኝም ከአዲስ አበባ 520 ኪ.ሜ፣ ከባህርዳር 360 ኪ.ሜ፣ ከላልይበላ 168 ኪ.ሜ፣ ከመቀሌ 260ኪ.ሜ፣ ከጅቡቲ ወደብ (በአፋር በኩል) 553 ኪ.ሜ እርቀትየተነሱ ሁሉ የሚገናኙባት ናት፡፡ በተጨማሪም በአሁኑ ወቅትየራስ ወሌ ብጡል ቤተ-መንግሥት በነበረበት በመርጦአቅጣጫ እዜት በርን አቋርጦ በመገንባት ላይ ያለውየደላንታ መንገድም ከተማዋን በማማከል 5ኛ ሀገርአቋራጭ መንገድ መሃል ከተማዋን ያቋርጣል፡፡

ታሪክ

ከተማው በታሪካዊ ቦታወች የተከበበ ሲሆን በ1834ዓ.ም. ወልደያን ጎብኝቶ የነበረው ሚስዮኑ ጆዓን ሉዊግ ክራፍ ደጅአዝማች ፋሪስ አሊጋዝ እና ወንድሙ እና ካሊድ ብሩ አሊጋዝ መምሪያቸውን በዚሁ ቦታ አድርገው እንደነበር ዘግቦት ይግኛል። ሁለቱ ወንድማማቾች በዚያን ወቅት ወረ ይመኑን ለመውጋት ተንቀሳቅሰው እንደነበር ይገልጻል፡፡[2]

በ1880ዎቹ ወልደያ ለዝሆን አደን ተስማሚ ስለነበር በታሪክ ተጠቃሽነት አለው። ከ1880ዎቹ እስከ 1950ዎቹ ወልደያ የየጁ አውራጃ ማዕከል ነበር[1]። በዚህ ወቅት፣ የወልደያ ሆስፒታል በ1929 ዓ.ም በኮንተራክተሩ M.C.M. Pollera ተገነባ። ሆስፒታሉ ሰፊ ቦታ የያዘና ለሰራተኞች ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ያለውም ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሆሰፒታሉ ለከተማው ነዋሪና ለተጎራባች ከተሞች (ላሊበላ፣ አላማጣ፡አፋር፣ ጎንደር) ከፍተኛ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተማዋ ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ግንባታ የሚታይባት ስትሆን በሶስት አቅጣጫ የሚነሱት አውራ መንገዶቹዋም በአስፓልት ኮንክሪት የተሰሩ ናቸው፡፡ የ ፪፬ ሰዓት የ ሀይድሮ ኤሌክትሪክ ፓዎር የምታገኝ ሲሆን በቅርቡ ደግሞ አንድ ዘመናዊ ስታዲዮም ለመስራት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡ በከተማዋ ውስጥ ባጃጅ ታክሲዎች በአሁኑ ጊዜ ዋነኞቹ የህዝብ ትራንስፖርት መንገዶች ናቸው፡፡

መልክዓ-ምድር እና የሥነ-ህዝብ ምጣኔ

የከተማዋ መልክዓ-ምድር አቀማመጥ ወጣ ገባና በተፈጥሮ በተራራ የተከበበች፣ ጥቁር ውሃ እና አላውሃ በዙሪያዋ የሚፈሱባት ስትሆን አጠቃላይ የቆዳ ስፋቷ ምጣኔም12,213.56 ሄክታር ሲሆን ከዚህ ውስጥ 6,445 በአሁኑ ማስተር ፕላን የፕላን ምድብ የተካተተ ነው፡፡ከምድረ ወገብ በ11,050 ሰሜን ኬክሮስናከ39,046 ምስራቅ ኬንትሮስ መካከል ስትገኝ ከባህርጠለል በላይ 2,112 ሜትር ከፍታ አላት፡፡ የዓየር ንብረቷም1% ደጋማ፣ 5% ቆላማ፣ 94% ወይና ደጋ ነው::

በ ከመሬት መቀማት ጋር በተነሳ የቀዳማዊ ወያኒ አመጽ ተብሎ በሚታወቀው የ1940 አመጽ ከተማው ላይ በየጁወች ጥቃት ሲደረስ፣ እስር ቤቱ ተከፍቶ እሰረኞች ተለቀቁ። ሆኖም አመጹ የተሳካ አልነበረም [3] አለም አቀፍ ሃብታም በመሆኑ የሚታወቀው መሀመድ አላሙዲ በ1950ወቹ ለ10 አመት በወልደያ እንዳደገ ይጠቀሳል። ጥቅምት 8-9፣ 1980 ከተማዋ በደርግ አውሮፕላን ብትደበደብም የሞተ ሰው ግን አልተዘገበም።[4]

ከዚህ በተረፈ ወልደያ ላይ የሚገኙት አኖማ ማርያም (በዛፎች ተሸሽጎ ዋሻ ውስጥ የተደበቀ ቤ/ክርስቲያን[5]) እና ወልደያ ገብርኤል ለአካባቢው ታዋቂነትን ይሰጣሉ። ገነተ ማርያምም ከወልደያ ብዙ ሳይርቅ ይገኛል።

የሕዝብ ስብጥር

በ 2007 በተደረገው አጠቃላይ የህዝብ ቆጠራ፣ የከተማዋ የህዝብ ብዛት 46,139 ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 23,000 ወንዶችና 23,139 ሴቶች ናቸው።[6]

የወልደያ ሕዝብ ቁጥር [7]
ዓ.ም.**የሕዝብ ብዛትየተማሪዎች ብዛት
1959
8,505
1976
15,700
1984
24,500
1993
30,200
1998
42,700
2007
46,139

ምንጮች