ኻሙዲ

==

ኻሙዲ
ምናልባት ኻሙዲ የሚል ማኅተም?
ምናልባት ኻሙዲ የሚል ማኅተም?
የግብጽ (ሂክሶስ) ፈርዖን
ግዛት1560-1548 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚአፐፒ
ተከታይ(1 አሕሞስ)
ሥርወ-መንግሥት15ኛው ሥርወ መንግሥት

==


ኻሙዲጥንታዊ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን የ15ኛው ሥርወ መንግሥት (ሂክሶስ) ፈርዖን ነበር።

ስሙ ከቶሪኖ ከፈን ፈርዖኖች ዝርዝርና በኢያሪኮ (ከነዓን ወይም እስራኤል) ከተገኙ ፪ ጥንዚዞች ታውቋል። እንዲሁም ምናልባት ከጌባል ፊንቄ የወጣ ማኅተም በአንዳንድ መምህር ዘንድ «ኻሙዲ» ይላል፣ ሌሎች ግን «ኻንዲ» እንደሚል ይመስላቸዋል።

የራይንድ ሥነ ቁጥራዊ ፓፒሩስ የተባለው ሰነድ ከአፐፒ ዘመን በኋላ በሚከተለው ፈርዖን 11ኛው ዓመት «የደቡብ ንጉሥ» (1 አሕሞስ) ወርሮ ወደ አቫሪስ እንደ ቀረበ ያመልክታል። አሁን ይህ የኻሙዲ 11ኛው ዓመት ማለት እንደ ነበር፣ አቫሪስም ከዚያ ቶሎ እንደ ወደቀ ይታስባል። አቫሪስ ከወደቀ በኋላ ሂክሶስ (አሞራውያን ወገን ሁነው) በዕብራውያን ነገደ ስምዖን ርስት ወደ ነበረው ወደ ሻሩሄን ሸሽተው አሕሞስ በዚያ ለ፫ ዓመት ያህል እንደ ከበባቸው ይታወቃል።

ቀዳሚው
አፐፒ
ግብፅ (ሂክሶስ) ፈርዖን
1560-1548 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
(1 አሕሞስ)