ካፍ
ከ ኩ ኪ ካ ኬ ክ ኮ ኳ ኰ ኲ ኴ ኵ
የአቡጊዳ ታሪክ | |||||
---|---|---|---|---|---|
አ | በ | ገ | ደ | ||
ሀ | ወ | ዘ | ሐ | ጠ | የ |
ከ | ለ | መ | ነ | ሠ | ዐ |
ፈ | ጸ | ቀ | ረ | ሰ | ተ |
ካፍ በጥንታዊ አቡጊዳ ተራ 11ኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያ በዕብራይስጥ በሶርያም ፊደሎች 11ኛው ፊደል "ካፍ" ይባላል። በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል "ካፍ" ተብሎ በ"አብጃድ" ተራ 11ኛ ነው።
በአማርኛ "ኸ ኹ ኺ ኻ ኼ ኽ ኾ" ከ"ከ..." ትንሽ ተቀይሯል።
ታሪክ
ተመሳሳይ ግብፃዊ ስዕል ("ደ") | ቅድመ-ሴማዊ | ሣባ | ግዕዝ | ||
---|---|---|---|---|---|
| ከ |
የካፍ መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የመዳፍ ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። አጠራሩ ግን "ደ" ነበር። በግብፅ የሠሩት ሴማውያን ግን በቋንቋቸው "ካፍ" ስላሉት፣ ይህ ስዕል "ክ" ሆኖ እንዲሰማ መጣ።
ከነዓን | አራማያ | ዕብራይስጥ | ሶርያ | ዓረብኛ |
---|---|---|---|---|
כ,ך | ﻙ |
የከነዓን "ካፍ" እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ የአረብኛም "ካፍ" ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት "ካፓ" (Κ, κ) አባት ሆነ። እሱም የላቲን አልፋቤት (K k) እና የቂርሎስ አልፋቤት (К к) ወላጅ ሆነ። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የ"ካፍ" ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር ፳ (ሃያ) ከግሪኩ κ በመወሰዱ እሱም የ"ከ" ዘመድ ነው።
🔥 Top keywords: ዋናው ገጽልዩ:Searchስዕል:Keristo1.pdfኢትዮጵያሚካኤል2ኛው ዓለማዊ ጦርነትሥርዓተ ነጥቦችፋይዳ መታወቂያሥነ-ፍጥረትአበበ ቢቂላአማርኛዓፄ ቴዎድሮስSpecial:Searchእርዳታ:ይዞታገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችውክፔዲያጥላሁን ገሠሠቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴኤችአይቪልዩ:RecentChangesየአድዋ ጦርነትግራኝ አህመድኃይሌ ገብረ ሥላሴሀዲስ ዓለማየሁየቅድስት ድንግል ማርያም ስሞችመጽሐፍ ቅዱስሥላሴየዋና ከተማዎች ዝርዝርአፋር (ክልል)የቃል ክፍሎችበዓሉ ግርማኢየሱስቅዱስ ጊዮርጊስ (ሰማዕት)አዲስ አበባቅዱስ ያሬድትግራይ ክልልእስራኤልየኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን