ኢንካ መንግሥት
የኢንካ መንግሥት ከ1430 እስከ 1525 በደቡብ አሜሪካ በተለይም ፔሩ የነበረ መንግሥት ነው።
![](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/a/a7/Inca_Expansion.svg/300px-Inca_Expansion.svg.png)
![](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/2/25/Sacsayhuaman_%28pixinn.net%29.jpg/350px-Sacsayhuaman_%28pixinn.net%29.jpg)
ቀድሞ በአንዴስ ተራሮች የነበሩት መንግሥታት የቲዋናኩ መንግሥት (300-1150 ዓም ግድም) እና የዋሪ መንግሥት (600-1100 ዓም ግድም) እንደ ተገኙ ታውቋል። ከነዚህ መንግሥታት ውድቀት በኋላ ከተነሡት አነስተኛ ክፍላገራት አንዱ የቁስቁ መንግሥት በ1190 ዓም ግድም ተነሣ። ይህ የቁስቁ መንግሥት በ1430 ዓም የኢንካ መንግሥት ተብሎ ጎረቤቶቹን በመያዝ መስፋፋት ጀመር። የኢንካ መንግሥት ስም በራሱ ቋንቋ በቀቿ «ታዋንቲንሱዩ» («አራቱ አውራጆች») ተባለ።
በ1518 ዓም የእስፓንያ አለቃ ፍራንሲስኮ ፒዛሮ ከነሥራዊቱ ጎበኛቸውና ወደ እስፓንያ ተመለሰ። የእስፓንያ ንግሥት እንዲወርራቸው ፈቃዷን ሰጥታ፣ ይህ ወረራ በ1524 ዓም ተከሠተ። ፒዛሮ በተመለሰበትም ጊዜ ኢንካዎች ከ1521 ዓም ጀምሮ በእርስ በርስ ጦርነት እንደ ተያዙ አገኛቸው። በዚህ ብሔራዊ ትግል ደክመውና ጠመንጃ ባለመኖራቸው ቶሎ ወደቁ። ሆኖም ቅሬታው አዲሱ ኢንካ መንግሥት እስከ 1564 ዓም ድረስ ቆየ።
🔥 Top keywords: ዋናው ገጽልዩ:Searchስዕል:Keristo1.pdfኢትዮጵያሚካኤል2ኛው ዓለማዊ ጦርነትሥርዓተ ነጥቦችፋይዳ መታወቂያሥነ-ፍጥረትአበበ ቢቂላአማርኛዓፄ ቴዎድሮስSpecial:Searchእርዳታ:ይዞታገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችውክፔዲያጥላሁን ገሠሠቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴኤችአይቪልዩ:RecentChangesየአድዋ ጦርነትግራኝ አህመድኃይሌ ገብረ ሥላሴሀዲስ ዓለማየሁየቅድስት ድንግል ማርያም ስሞችመጽሐፍ ቅዱስሥላሴየዋና ከተማዎች ዝርዝርአፋር (ክልል)የቃል ክፍሎችበዓሉ ግርማኢየሱስቅዱስ ጊዮርጊስ (ሰማዕት)አዲስ አበባቅዱስ ያሬድትግራይ ክልልእስራኤልየኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን