አራት

አራት በተራ አቆጣጠር ከሦስት የሚከተለው ቁጥር ነው።

ምልክቱ ከግዕዝ እንደ ተወረሰ ነው፣ ይህም ከግሪክ አልፋቤት ፬ኛው ፊደል ደልታ (በትልቁ «Δ») እንደ ተወሰደ ይታመናል።

ከሕንዳዊ ላሳናት 4 ምልክቶች ወደ ዘመናዊ «4» የደረሱ ለውጦች።

በብዙ ልሳናት የሚገኘው ምልክት 4 ከሕንዳዊ ቁጥር ምልክቶች ተደረጀ። እነዚህ ምልክቶች በአውሮፓ ከ968 እና 1550 ዓም መካከል እየተደረጁ ተቀባይነት አገኙ። ከዚያ አስቀድሞ በሮማውያን ቁጥር ምልክቶች የ«አራት» ምልክት «IV» (ወይም «iv») ነበር።