ላዊ
ለ ሉ ሊ ላ ሌ ል ሎ ሏ
የአቡጊዳ ታሪክ | |||||
---|---|---|---|---|---|
አ | በ | ገ | ደ | ||
ሀ | ወ | ዘ | ሐ | ጠ | የ |
ከ | ለ | መ | ነ | ሠ | ዐ |
ፈ | ጸ | ቀ | ረ | ሰ | ተ |
ላዊ (ወይም ላዌ፥ ለው) በጥንታዊ አቡጊዳ ተራ 12ኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያ በዕብራይስጥ በሶርያም ፊደሎች 12ኛው ፊደል «ላሜድ» ይባላል። በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል «ላም» ተብሎ በ«አብጃድ» ተራ 12ኛ ነው።
ታሪክ
ተመሳሳይ ግብፃዊ ስዕል | ቅድመ-ሴማዊ | ሣባ | ግዕዝ | ||
---|---|---|---|---|---|
| ለ |
የላዊ መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የቅዝምዝም ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። አጠራሩ ግን «ዐወት» ነበር። በግብፅ የሠሩት ሴማውያን ግን በቋንቋቸው «ላሜድ» ስላሉት፣ ይህ ስዕል «ል» ሆኖ እንዲሰማ መጣ።
ከነዓን | አራማያ | ዕብራይስጥ | ሶርያ | ዓረብኛ |
---|---|---|---|---|
ל | ﻝ |
የከነዓን «ላሜድ» እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ «ላሜድ» የአረብኛም «ላም» ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት «ላምብዳ» (Λ, λ) አባት ሆነ። እሱም የላቲን አልፋቤት (L l) እና የቂርሎስ አልፋቤት (Л л) ወላጅ ሆነ። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የ«ላዊ» ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር ፴ (ሠላሳ) ከግሪኩ Λ በመወሰዱ እሱም የ«ለ» ዘመድ ነው።
🔥 Top keywords: ዋናው ገጽልዩ:Searchስዕል:Keristo1.pdfኢትዮጵያሚካኤል2ኛው ዓለማዊ ጦርነትሥርዓተ ነጥቦችፋይዳ መታወቂያሥነ-ፍጥረትአበበ ቢቂላአማርኛዓፄ ቴዎድሮስSpecial:Searchእርዳታ:ይዞታገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችውክፔዲያጥላሁን ገሠሠቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴኤችአይቪልዩ:RecentChangesየአድዋ ጦርነትግራኝ አህመድኃይሌ ገብረ ሥላሴሀዲስ ዓለማየሁየቅድስት ድንግል ማርያም ስሞችመጽሐፍ ቅዱስሥላሴየዋና ከተማዎች ዝርዝርአፋር (ክልል)የቃል ክፍሎችበዓሉ ግርማኢየሱስቅዱስ ጊዮርጊስ (ሰማዕት)አዲስ አበባቅዱስ ያሬድትግራይ ክልልእስራኤልየኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን